Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ሞ​ንም ልጆች አለ​ቆች ጌታ​ቸ​ውን ሐኖ​ንን፥ “ዳዊት አባ​ት​ህን በፊ​ትህ ለማ​ክ​በር አጽ​ና​ኞ​ችን ወደ አንተ የላከ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ዳዊ​ትስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ሰ​ለል፥ ለመ​ፈ​ተ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን የላከ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የአሞናውያን መኳንንት ጌታቸውን ሐኖንን፣ “ዳዊት የተሰማውን ሐዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር ዐስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፣ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የአሞናውያን መኳንንት፥ ጌታቸው ሐኑንን፥ “ዳዊት የተሰማውን ኀዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር አስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፥ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የዐሞናውያን መሪዎች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላካቸው በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል ያመች ዘንድ እንዲሰልሉለት አይደለምን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የአሞንም ልጆች አለቆች ጌታቸውን ሐኖንን፦ ዳዊት አባትህን አክብሮ ሊያጽናናህ ባሪያዎቹን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ዳዊትስ ከተማይቱን ለመመርመርና ለመሰለል ለማጥፋትም ባሪያዎቹን የላከ አይደለምን? አሉት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 10:3
6 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ያመጣ ዘንድ ከእ​ና​ንተ አን​ዱን ላኩ፤ እና​ንተ ግን እው​ነ​ትን የም​ት​ና​ገሩ ከሆነ ወይም ከአ​ል​ሆነ ነገ​ራ​ችሁ እስ​ኪ​ታ​ወቅ ድረስ ከዚህ ተቀ​መጡ፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ሰላ​ዮች ናችሁ።”


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ፤ የሀ​ገ​ሩን ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።”


የኔር ልጅ አበ​ኔር ያታ​ል​ልህ ዘንድ፥ መው​ጫ​ህ​ንና መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ያውቅ ዘንድ ፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ እንደ መጣ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው።


የአ​ሞን ልጆች አለ​ቆች ግን ሐና​ንን፥ “ዳዊት የሚ​ያ​ጽ​ና​ኑ​ህን ወደ አንተ የላከ አባ​ት​ህን በማ​ክ​በር ነውን? አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ሀገ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ሰ​ለል ወደ አንተ የመጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?” አሉት።


ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤ አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም።


በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos