Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ሞን ልጆች አለ​ቆች ግን ሐና​ንን፥ “ዳዊት የሚ​ያ​ጽ​ና​ኑ​ህን ወደ አንተ የላከ አባ​ት​ህን በማ​ክ​በር ነውን? አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ሀገ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ሰ​ለል ወደ አንተ የመጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን፣ “ዳዊት ሐዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃልን? ሰዎቹ ወደ አንተ የመጡት አገሪቱን ለመመርመር፣ ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የአሞን ልጆች ሹማምንት ግን ሐኖንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባርያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዐሞናውያን ባለሥልጣኖች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላከው ምድሪቱን ወሮ መያዝ ይችል ዘንድ እንዲሰልሉለት ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐኖንን “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባሪያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 19:3
12 Referencias Cruzadas  

የአ​ሞ​ንም ልጆች አለ​ቆች ጌታ​ቸ​ውን ሐኖ​ንን፥ “ዳዊት አባ​ት​ህን በፊ​ትህ ለማ​ክ​በር አጽ​ና​ኞ​ችን ወደ አንተ የላከ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ዳዊ​ትስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ሰ​ለል፥ ለመ​ፈ​ተ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን የላከ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።


ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ወረታ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ናን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያ​ጽ​ና​ናው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ሊያ​ጽ​ና​ኑት ወደ ሐናን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።


ሐና​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ግማሽ አስ​ላ​ጫ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ለሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።


የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን በእ​ርሱ ላይ ተቈ​ጥ​ተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመ​ጣ​ህ​በት ቦታ መል​ሰው፤ በሰ​ል​ፉም ውስጥ ጠላት እን​ዳ​ይ​ሆ​ነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ው​ረድ፤ ከጌ​ታው ጋር በምን ይታ​ረ​ቃል? የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ራስ በመ​ቍ​ረጥ አይ​ደ​ለ​ምን?


አን​ኩ​ስም መልሶ ዳዊ​ትን፥ “በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ወ​ጣም’ አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos