ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
ኢያሱ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ኤፍሬማውያን ግን በጌዜር የሚኖሩ ከነዓናውያንን አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህም ከነዓናውያን እስከ አሁን ድረስ በኤፍሬማውያን መካከል ይኖራሉ፤ ሆኖም ለኤፍሬማውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፥ የጉልበት ግብርም ያስገብሩአቸው ነበር። |
ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጋዜርን ያዘ፤ በእሳትም አቃጠላት፤ በሜርጎብ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንንም ገደላቸው፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት እነዚያን አገሮች ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር።
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸውም በምድር ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አደረጋቸው።
በዚያ ጊዜም የጋዜር ንጉሥ ኤላም ላኪስን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር በሰይፍ ስለት እርሱንና ሕዝቡን መታ፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
የምናሴ ልጆችም የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ማጥፋት ተሳናቸው፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያች ሀገር ለመቀመጥ መጡ።
ኤፍሬምም በጋዜር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው በጋዜር ተቀመጡ፤ ገባሮችም ሆኑላቸው።