La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለ​ውን ምድር ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና አሁን ደግሞ የው​ኃ​ውን ምን​ጭ ስ​ጠኝ” አለ​ችው። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ው​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ምንጭ ሰጣት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጕድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷም እንዲህ አለችው፦ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ።” እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 15:19
8 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።


የይ​ሁ​ዳም በረ​ከት ይህች ናት፤ አቤቱ የይ​ሁ​ዳን ቃል ስማ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ይግባ፤ እጆ​ቹም ይግዙ፤ በጠ​ላ​ቶቹ ላይ ረዳት ትሆ​ነ​ዋ​ለህ።


እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።


በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።


አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።