Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሷም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፤ እርሷም ከአህያዋ ወረደች፤ ካሌብም፦ “ምን ፈለግሽ?” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፥ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 15:18
4 Referencias Cruzadas  

ርብ​ቃም ዓይ​ኖ​ች​ዋን አቀ​ናች፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም አየች፤ ከግ​መ​ልም ወረ​ደች።


እር​ስ​ዋም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለ​ውን ምድር ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና አሁን ደግሞ የው​ኃ​ውን ምን​ጭ ስ​ጠኝ” አለ​ችው። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ው​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ምንጭ ሰጣት።


እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ የእ​ርሻ ቦታ ይሰ​ጣት ዘንድ አባ​ቷን እን​ድ​ት​ለ​ም​ነው ጎቶ​ን​ያል መከ​ራት። እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና አን​ጐ​ራ​ጐ​ረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድ​ደ​ኸ​ኛል” ብላም ጮኸች። ካሌ​ብም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት።


አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos