ኢያሱ 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በላከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬም ገና እንዲሁ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጽኑዕ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም ዐብሮኝ አለ፤ ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድ፣ ለመውጣትም ለመግባትም ኀይሉም ብርታቱም አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። |
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
አላቸውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ‘ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል።
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመታት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።