Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም ዐብሮኝ አለ፤ ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድ፣ ለመውጣትም ለመግባትም ኀይሉም ብርታቱም አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴም በላ​ከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበ​ርሁ፥ ዛሬም ገና እን​ዲሁ ለመ​ዋ​ጋት ለመ​ው​ጣ​ትም ለመ​ግ​ባ​ትም ጽኑዕ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 14:11
7 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።


አላቸውም፦ እኔ ዛሬ መቶ ሀያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል።


ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤ 2 እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፤ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም።


አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፥ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos