አህያውንም አስጭና ሎሌዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ቄርሜሎስ ተራራ እንሂድ” አለችው።
ኢያሱ 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፥ “ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው ሀገር የሚኖሩ የአሞሬዎናውያን ነገሥት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድነንም፤ ርዳንም፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገባዖንም ሰዎች በጌልገላ ወደ ሰፈረው ወደ ኢያሱ፣ “በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው ተሰልፈውብናል፤ እኛን ባሮችህን አትተወን፤ ርዳን፤ ፈጥነህ በመድረስም አድነን” ሲሉ ላኩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገባዖን ሰዎችም ሰፈሩን በጌልገላ አድርጎ ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት፦ “በተራራማው አገር የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ እኛን ሊወጉን ስለ ተባበሩብን እኛ አገልጋዮችህን ችላ አትበል! በቶሎ ወደ እኛ ወጥተህ እርዳንና አድነን!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፦ ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፥ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም አሉት። |
አህያውንም አስጭና ሎሌዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ቄርሜሎስ ተራራ እንሂድ” አለችው።
በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥ አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤ በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ።
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”
ከእናንተም ጥበበኞችና ዐዋቂዎች፥ አስተዋዮችም የሆኑትን ሰዎች ወሰድሁ፤ በእናንተም ላይ አለቆች፥ የሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የአምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም፥ ለፈራጆቻችሁም ጻፎች አድርጌ ሰየምኋቸው።
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
የኤናቅ ልጆች ከተማ ቅርያትያርቦቅንና በዙሪያዋ ያሉ መሰማሪያዎችን ሰጡአቸው፤ ይህችውም በይሁዳ ተራራ ያለች ኬብሮን ናት።
የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ።
ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ሰላም አደረገ፤ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።
ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ጉባኤ ወደ ጌልገላ መጥተው ለኢያሱና ለእስራኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥተናል፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ” አሉ።
ኢያሱንም፥ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገርም ነን” አሉት። ኢያሱም፥ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?” አላቸው።