Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አህ​ያ​ው​ንም አስ​ጭና ሎሌ​ዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላ​ዝ​ዝህ አታ​ዘ​ግ​የኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ቄር​ሜ​ሎስ ተራራ እን​ሂድ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም አህያውን ጭና አገልጋይዋን፣ “ቶሎ ቶሎ ንዳ፤ እኔ ካልነገርኩህ በቀር ለእኔ ብለህ አታዝግም” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሷም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አህያውንም አስጭና ሎሌዋን “ንዳ፤ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤” አለችው።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 4:24
7 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


ልጆ​ቹ​ንም፥ “አህ​ያ​ዬን ጫኑ​ልኝ” አላ​ቸው፥ አህ​ያ​ው​ንም ጫኑ​ለት ተቀ​መ​ጠ​በ​ትም።


እን​ጀ​ራም ከበላ፥ ውኃም ከጠጣ በኋላ ለተ​መ​ለ​ሰው ነቢይ አህ​ያ​ውን ጫኑ​ለት።


እር​ሱም፥ “መባቻ ወይም ሰን​በት ያይ​ደለ ዛሬ ለምን ትሄ​ጃ​ለሽ?” አለ። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።


እን​ዲ​ሁም ሄደች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ወጣች። ኤል​ሳ​ዕም ያችን ሴት ወደ እርሱ ስት​መጣ ባያት ጊዜ ሎሌ​ውን ግያ​ዝን፥ “እነ​ኋት፥ ሱማ​ና​ዊት መጣች፤


ሙሴም ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን ወሰደ፤ በአ​ህ​ዮች ላይም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤ ወደ ግብ​ፅም ሀገር ተመ​ለሰ፤ ሙሴም ያችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በትር በእጁ ይዞ ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos