Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፦ ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፥ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የገባዖንም ሰዎች በጌልገላ ወደ ሰፈረው ወደ ኢያሱ፣ “በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው ተሰልፈውብናል፤ እኛን ባሮችህን አትተወን፤ ርዳን፤ ፈጥነህ በመድረስም አድነን” ሲሉ ላኩበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የገባዖን ሰዎችም ሰፈሩን በጌልገላ አድርጎ ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት፦ “በተራራማው አገር የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ እኛን ሊወጉን ስለ ተባበሩብን እኛ አገልጋዮችህን ችላ አትበል! በቶሎ ወደ እኛ ወጥተህ እርዳንና አድነን!”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 10:6
14 Referencias Cruzadas  

አህያውንም አስጭና ሎሌዋን “ንዳ፤ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤” አለችው።


እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፥ እርሱ ያድነናል።


በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።


ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥


ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች መረጥሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች የሻለቆችም የመቶ አለቆችም የአምሳ አለቆችም የአሥር አለቆችም ገዦችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።


አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ።


በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰምርያ ሰጡአቸው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፥ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።


ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ሰላም አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፥ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።


ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች፦ ከሩቅ አገር መጥተናል፥ አሁንም ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።


ኢያሱንም፦ እኛ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ኢያሱም፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ? አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos