La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ቄዳ ወደ ልብና አለፉ፤ ልብ​ና​ንም ወጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከመቄዳ ወደ ልብና ዐለፉ፤ ወጓትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ፥ ልብናንም ወጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ ከማቄዳ ሄደው በሊብና ላይ አደጋ ጣሉባት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ፥ ልብናንም ወጉ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:29
14 Referencias Cruzadas  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በሎ​ምና ሲዋጋ አገ​ኘው።


ኤዶ​ም​ያስ ግን ለይ​ሁዳ እን​ዳ​ይ​ገ​ብር እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ላይ ሸፈተ። በዚ​ያም ዘመን ደግሞ የሎ​ምና ሰዎች ሸፈቱ።


ኤዶ​ም​ያስ ግን በይ​ሁዳ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፀ፤ በዚ​ያም ዘመን ልብና ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ዐመፀ፤ የአ​ባ​ቶ​ቹን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትቶ ነበ​ርና።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በል​ብና ሲዋጋ አገ​ኘው።


ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ከሬ​ሞት ዘፋ​ሬ​ስም ተጕ​ዘው በል​ብና ሰፈሩ።


በዚ​ያም ቀን መቄ​ዳን ያዟት፤ እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ሩም፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረጉ በመ​ቄዳ ንጉሥ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በል​ብና ንጉሥ አደ​ረገ።


የል​ብና ንጉሥ፥ የዓ​ዶ​ላም ንጉሥ፥


ሌምና፥ ኤተቅ፥ አኖክ፥


ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥


ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ፥ ከወ​ንድ እስከ ሴት፥ ከሕ​ፃን እስከ ሽማ​ግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።


በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።