ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ዮናስ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራሮች መሠረት ወረደ፤ ከጥንት ጀምሮ መወርወሪያዎችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረድሁ፤ አቤቱ ፈጣሪዬ! ሕይወቴ ጥፋት ሳያገኛት ወዳንተ ትውጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕይወቴ እየተዳከመ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔርን አስታወስኩ፤ ወደ አንተ ወደ አምላኬ ጸለይኩ፤ ጸሎቴም ወደ ቤተ መቅደስህ ወደ አንተ መጣ። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።