ዮናስ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆች እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር ከበበኝ፥ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠመጠመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ። |
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝሩ የለካ፥ ምድርንም ሁሉ ሰብስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፥ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር ወደ ቀደሙት ሕዝብ አወርድሻለሁ። በምድርም ላይ በሕይወትሽ ጸንተሽ እንዳትኖሪም ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈረሰው ቤት ከምድር በታች አኖርሻለሁ።
በውኃው አጠገብ ያሉ የዕንጨቶች ሁሉ ቁመት እንዳይረዝም ራሱም ወደ ደመና እንዳይደርስ ያንም ውኃ የሚጠጡት እንጨቶች ሁሉ በርዝመታቸው ከእርሱ ጋራ እንዳይተካከሉ ሁሉም ወደ መቃብር በሚወርዱ ሰዎች መካከል በጥልቅ ምድር ሞቱ።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።