የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ “ ‘ከሰማይ’ ብንል ‘እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
ዮሐንስ 8:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ኀጢኣት ከእናንተ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እኔ እውነት የምናገር ከሆንሁ ለምን አታምኑኝም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ስለ ኀጢአት በማስረጃ ሊከስሰኝ የሚችል አለን? እውነት የምናገር ከሆነ፣ ለምን አታምኑኝም? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለምን አታምኑኝም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ከእናንተ ‘ኃጢአተኛ ነህ’ ብሎ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆንኩ ታዲያ፥ ለምን አታምኑኝም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም? |
የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ “ ‘ከሰማይ’ ብንል ‘እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
ጲላጦስም፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል” አለው።
ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ ስለዚህ እናንተ አትሰሙኝም፤ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና።”
ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።