መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ዮሐንስ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ለምናውቀው እንሰግዳለን፤ መድኀኒት ከአይሁድ ወገን ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው እንሰግዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ለማታውቁት አምላክ ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚመጣው ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው አምላክ እንሰግዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
በዚህም ሳልፍ ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሕፈት ያለበትን የምታመልኩበትን መሠዊያችሁን አየሁ፤ እነሆ፥ እኔ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እገልጽላችኋለሁ።
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።
እግዚአብሔርም አስቀድሞ ልጁን አስነሣላችሁ፤ ሁላችሁም ከክፋታችሁ እንድትመለሱ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”