Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጌታ​ችን ከይ​ሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የተ​ገ​ለጠ ነውና፤ ስለ​ዚ​ህም ነገድ ሙሴ ምንም እን​ኳን ስለ ክህ​ነት አል​ተ​ና​ገ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ መጣ ግልጽ ነውና፤ ሙሴ ስለ ካህናት ሲናገር ይህን ነገድ አስመልክቶ የተናገረው ምንም ነገር የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የታወቀ ነው፤ ከዚያ ነገድ ጋር በተገናኘ ስለ ካህናት ሙሴ ምንም አልተናገረም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑ የታወቀ ነው፤ ሆኖም ሙሴ ስለ ካህናት ሲናገር የይሁዳን ነገድ አስመልክቶ የተናገረው ምንም ነገር የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 7:14
22 Referencias Cruzadas  

አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


ከእ​ሴይ ሥር በትር ትወ​ጣ​ለች፤ አበ​ባም ከግ​ንዱ ይወ​ጣል።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ፥ የአ​ራም ልጅ፥ የኦ​ርኒ ልጅ፥ የኤ​ስ​ሮም ልጅ፥ የፋ​ሬስ ልጅ፤ የይ​ሁዳ ልጅ፥


“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”


ከዳ​ዊት ዘር ሰው ሆኖ በሥጋ ስለ ተወ​ለደ ስለ ልጁ፥


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይ​ተህ የም​ት​ጠ​ላ​ው​ንና የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ውን ያን አንተ ራስህ የም​ት​ሠ​ራው ከሆነ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ ታስ​ባ​ለ​ህን?


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ።


እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


የጌ​ታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ?


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አው​ናን በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የፋ​ሬ​ስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስ​ሮም፥ ይሞ​ሔል፤


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


ይህ ነገር የተ​ነ​ገ​ረ​ለት እርሱ በሌላ ወገን ተካ​ፍ​ሎ​አ​ልና፥ ከዚ​ያም መሠ​ዊ​ያ​ውን ያገ​ለ​ገለ ማንም የለም።


ይል​ቁ​ንም ይህ እጅግ ያስ​ረ​ዳል፤ በመ​ልከ ጼዴቅ ክህ​ነት አም​ሳል ሌላ ካህን ይነ​ሣል ብሎ​አ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios