La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 19:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ሆም​ጣጤ የመ​ላ​በት ማሰሮ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ሆም​ጣ​ጤ​ውን በሰ​ፍ​ነግ ሞል​ተው በስ​ምዛ ዘንግ ከአፉ አገ​ና​ኝ​ተው ጨመ​ቁት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያም የኮመጠጠ ወይን የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሰፍነግ በወይን ጠጅ ነክረው፣ በሂሶጵ ዘንግ ወደ አፉ አቀረቡለት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እዚያ ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ስለዚህ እዚያ የነበሩ ሰዎች፥ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞሉና በሂሶጵ እንጨት አንጠልጥለው ወደ አፉ አቀረቡለት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 19:29
9 Referencias Cruzadas  

ስለ ዛፍም ከሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅ​ጥር ግንብ ላይ እስ​ከ​ሚ​በ​ቅ​ለው እስከ አሽ​ክት ድረስ ይና​ገር ነበር፤ ደግ​ሞም ስለ አው​ሬ​ዎ​ችና ስለ ወፎች ስለ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና ስለ ዓሣ​ዎች ይና​ገር ነበር።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


ከሂ​ሶጵ ቅጠ​ልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለ​ውም ደም ንከ​ሩት፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ ከአ​ለው ደም ሁለ​ቱን መቃ​ኖ​ችና ጉበ​ኑን እርጩ፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ሰው እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይ​ውጣ።


ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።


በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።


ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፤ በመቃም አድርጎ አጠጣው።


ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።


አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎ “ተዉ፤ ኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ፤” እያለ አጠጣው።


ጭፍ​ሮ​ችም ይዘ​ብ​ቱ​በት ነበር፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው ሆም​ጣጤ አመ​ጡ​ለት።