Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 4:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ስለ ዛፍም ከሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅ​ጥር ግንብ ላይ እስ​ከ​ሚ​በ​ቅ​ለው እስከ አሽ​ክት ድረስ ይና​ገር ነበር፤ ደግ​ሞም ስለ አው​ሬ​ዎ​ችና ስለ ወፎች ስለ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና ስለ ዓሣ​ዎች ይና​ገር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሯል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታትና ስለ ዓሦችም ተናግሯል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ሰሎሞን ሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ ሂሶጵ ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ሰለተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 4:33
13 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ሦስት ሺህ ምሳ​ሌ​ዎ​ችን ተና​ገረ፤ መሐ​ል​ዩም አንድ ሺህ አም​ስት ነበረ።


ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥ ጥበ​ቡን ሰም​ተው ከነ​በሩ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ለመ​ስ​ማት ሰዎች ይመጡ ነበር።


አን​ተስ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ እጅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ተገ​ዳ​ደ​ርህ፤ እን​ዲ​ህም አልህ፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ጥግ እወ​ጣ​ለሁ፤ ረጃ​ጅ​ሞ​ች​ንም ዝግ​ባ​ዎች የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሩም ዳር​ቻና ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ዱር እገ​ባ​ለሁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


ከሂ​ሶጵ ቅጠ​ልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለ​ውም ደም ንከ​ሩት፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ ከአ​ለው ደም ሁለ​ቱን መቃ​ኖ​ችና ጉበ​ኑን እርጩ፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ሰው እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይ​ውጣ።


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።


እግ​ሮቹ በም​ዝ​ምዝ ወርቅ እንደ ተመ​ሠ​ረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰ​ሶ​ዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባ​ኖ​ስና እንደ ዝግባ ዛፍ የተ​መ​ረጠ ነው።


የዝ​ግ​ባ​ውን ዕን​ጨት፥ ሂሶ​ጱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ደኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ ወስዶ በታ​ረ​ደ​ችው ዶሮ ደምና በም​ንጩ ውኃ ውስጥ ይነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥ ቤቱ​ንም ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል።


ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።


እን​ደ​ሚ​ጋ​ርዱ ዛፎች፥ በወ​ንዝ ዳር እን​ዳሉ የተ​ክል ቦታ​ዎች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተከ​ላ​ቸው ድን​ኳ​ኖች በው​ኃም ዳር እን​ዳሉ ዝግ​ባ​ዎች ናቸው።


ሙሴ የኦ​ሪ​ትን ትእ​ዛዝ ሁሉ ለመ​ላው ሕዝብ ከነ​ገረ በኋላ፥ የላ​ምና የፍ​የል ደም ከውኃ ጋር ቀላ​ቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕ​ርና የስ​ሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽ​ሐፈ ኦሪ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos