አኪጦፌልም ምክሩ እንዳልሠራ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፤ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ኢዮብ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትን ከመንፈሴ ትለያለህ። አጥንቶቼንም ከሞት ትጠብቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣ መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ ሥጋ ይልቅ ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሥቃይ የበዛበት ሰውነት ተሸክሜ ከመኖር ታንቄ መሞትን እመርጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ መታነቅንና ሞትን መረጠች። |
አኪጦፌልም ምክሩ እንዳልሠራ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፤ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስን አዘዘ፤ ዮናስንም እስኪዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕይወት ሞት ይሻለኛል” አለ።