Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እን​ድ​ታ​ገሥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለ​ሁን? ሕይ​ወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሕይወቴን እጸየፋለሁ፤ ዘላለም መኖር አልፈልግም፤ ዘመኔ እንደ እስትንፋስ ነውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ተስፋ ቈርጬአለሁ፤ መኖርም አልፈልግም፤ የሕይወቴም ዘመን አጭር ስለ ሆነ ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘላለም ልኖር አልወድድም፥ የሕይወቴ ዘመን እስትንፋስ ነውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 7:16
22 Referencias Cruzadas  

“ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።


እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


አቤቱ፥ ታድ​ነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።


“እንደ ምን​ደኛ ሕይ​ወ​ቱን እን​ዲ​ጠ​ባ​በ​ቃት፥ ያርፍ ዘንድ ከእ​ርሱ ዘወር በል።


የሕ​ይ​ወቴ ዘመን አጭር አይ​ደ​ለ​ምን? ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤


ንጹሕ ነኝ፤ ራሴ​ንም አላ​ው​ቅም፤ ነገር ግን ሕይ​ወቴ ጠፋች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያቈ​ስ​ለኝ ዘንድ ጀመረ፥ ነገር ግን እስከ መጨ​ረ​ሻው አላ​ጠ​ፋ​ኝም።


አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”


የልጅ ልጆች ሥራ​ህን ያደ​ን​ቃሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይና​ገ​ራሉ፥


እነ​ርሱ ግን ነፍ​ሴን ለከ​ንቱ ፈለ​ጓት፤ ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።


ቅን​ነ​ት​ህን በልቤ ውስጥ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም፥ ማዳ​ን​ህ​ንም ተና​ገ​ርሁ፤ ይቅ​ር​ታ​ህ​ንና ምሕ​ረ​ት​ህን ከታ​ላቅ ጉባኤ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም።


ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”


ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።


ሕይ​ወ​ትን ከመ​ን​ፈሴ ትለ​ያ​ለህ። አጥ​ን​ቶ​ቼ​ንም ከሞት ትጠ​ብ​ቃ​ለህ።


እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”


መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።


ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios