ኢዮብ 38:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዝናብ አባቱ ማን ነው? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝናብ አባት አለውን? የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይም የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብንና ጤዛን የሚያስገኝ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? |
እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
በላይ በሰማይ ውኆችን ይሰበስባል፤ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
በልባቸውም፦ የመከሩንና የበልጉን ዝናብ በጊዜ የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።
እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ምግብን በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የበልጉንና የመከሩን ዝናብ ያዘንብላችኋልና።
መከር ሳይደርስ ገና ከሦስት ወር በፊት ዝናብን ከለከልኋችሁ፤ በአንድም ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ በአንድ ወገን ዘነበ፤ ያልዘነበበትም ወገን ደረቀ።
እስራኤልም ተማምኖ፥ በያዕቆብ ምድር ብቻውን፥ በስንዴና በወይን ምድር ይኖራል፤ ሰማይ ከደመናና ከጠል ጋር ለአንተ ነው።