ኢዮብ 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስክሞትም ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣ የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የተናገራችሁት ሁሉ ትክክል ነው ብዬ በፍጹም አልቀበልም፤ እስከምሞትበት ቀን ድረስ በቅንነት መጽናቴን አልተውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም። |
እግዚአብሔርም ሰይጣንን አለው፥ “በባሪያዬ በኢዮብ ላይ እንዲህ እንዳታስብ ተጠንቀቅ፤ በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድቅና ንጹሕ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ከክፋትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግመኛም ቅን የሆነ ሰው የለምና፤ አንተ ግን ሀብቱን በከንቱ አጠፋ ዘንድ ነገርኸኝ።”
ብዙ ወራትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እንዲህ አለችው፥ “እስከ መቼ ትታገሣለህ? 9 ‘ሀ’ ዳግመኛም እግዚአብሔርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠናዋለሁ፤ ዳግመኛም መከራውን እታገሠዋለሁ፤ የቀድሞው ኑሬዬንም ተስፋ አደርገዋለሁ ትላለህን? 9 ‘ለ’ እንደዚህስ እንዳትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠራርህ ጠፋ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅፀኔም በምጥ ተጨነቀ፥ በከንቱም ደከምሁ። 9 ‘ሐ’ አንተም በመግልና በትል ትኖራለህ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ትዛብራለህ። 9 ‘መ’ እኔ ግን እየዞርሁ እቀላውጣለሁ። ከአንዱ መንደር ወደ አንዱ መንደር፥ ከአንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄዳለሁ፤ ከድካሜና በእኔ ላይ ካለ ችግሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ እጠብቃለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግዚአብሔርን ስደብና ሙት።”
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
እግዚአብሔርም ይህን ቃል ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፥ “እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ አንዲት ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና አንተና ሁለቱ ባልንጀሮችህ በድላችኋል።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።