ኢዮብ 24:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠባብ ቦታ በዐመፅ ይሸምቃሉ፥ የጽድቅንም መንገድ አያውቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየተረተሩ የወይራ ዘይት ያወጣሉ፤ ወይን እየጠመቁ፣ ራሳቸው ግን ይጠማሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚህ ሰዎች አጥር ውስጥ ዘይት ያወጣሉ፥ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን ይጠማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉ ሰዎች የአትክልት ቦታ ከወይራ ፍሬ ዘይት ያወጣሉ፤ ከወይን ዘለላም የወይን ጠጅን ይጠምቃሉ፤ እነርሱ ግን ይጠማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚህ ሰዎች አጥር ውስጥ ዘይት ያደርጋሉ፥ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን ይጠማሉ። |
ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና።
ቤቱን በዐመፅ፥ አዳራሹንም ያለ እውነት ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው ወዮለት!