ኢዮብ 20:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእባብን መርዝ ይጠባል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእባብ መርዝ ይጠባል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፥ የእባብም ምላስ ይገድለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው የሚበላው ሁሉ መርዝ ይሆንበታል፤ መርዝም ሆኖ ይገድለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፥ የእባብም ምላስ ይገድለዋል። |
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ።