ኢዮብ 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተዋረዱ ሰዎች ልጆቹን ያጠፋሉ፤ እጆቹም የኀዘን እሳትን ያቀጣጥላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቹ ለድኾች ካሳ መክፈል አለባቸው፤ እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ ድሆቹን ይክሳሉ፥ በገዛ እጆቹ ሀብቱን ይመልሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹ እየተለማመጡ አባታቸው ከድኾች በግፍ የቀማውን ገንዘብ ይከፍላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ፥ እጁ ሀብቱን ይመልሳል። |
ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም።
እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጠ፤ እነርሱም አዋሱአቸው። እነርሱም ግብፃውያንን በዘበዙአቸው።
“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”