ኢዮብ 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመኖር ተስፋ አያደርግም፤ ፍጻሜው ከንቱ ይሆናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐጸፋው አንዳች አያገኝምና፤ ከንቱን ነገር በመታመን ራሱን አያታልል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከንቱ ነገር እየተማመነ ራሱን አያታል፤ በዚህም ዋጋ ቢስ ሆኖ ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልና ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን። |
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
ነፋስን ዘርተዋልና ዐውሎ ነፋስን አጨዱ፤ ለነዶአቸውም ኀይል የለውም፤ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም ጠላት ይበላዋል።
በከንቱ ነገርም የሚያስታችሁ አይኑር፤ በእርሱ ምክንያት በከሓዲዎች ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መዓት ይመጣልና።