ኢዮብ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢኣት ብሠራ አንተ ትጠባበቀኛለህ፤ ከኀጢኣቴም ንጹሕ አታደርገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአትን ብሠራ ትመለከተኛለህ፤ መተላለፌንም ሳትቀጣ አታልፍም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደል ብፈጽም አንተ ትመለከታለህ፤ ኃጢአቴንም ሳትቀጣ አታልፈውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም። |
የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
ለብዙ ሺህ ጽድቅን የሚጠብቅ፥ ቸርነትን የሚያደርግ፥ አበሳንና መተላለፍን፥ ኀጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኀጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው” ሲል አወጀ።
እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።