Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ስለ ምን መተ​ላ​ለ​ፌን ይቅር አት​ልም? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ስለ ምን አታ​ነ​ጻም? አሁን በም​ድር ውስጥ እተ​ኛ​ለሁ፤ በማ​ለ​ዳም አል​ነ​ቃም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም? ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሷል፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከቶ ኃጢአቴን ይቅር አትልልኝምን? የማደርገውንስ በደል አትደመስስልኝምን? ወደ መቃብር መውረጃዬ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ብትፈልገኝ እንኳ አልገኝም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለ ምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ማለዳ ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 7:21
29 Referencias Cruzadas  

ኀጢ​ኣት ብሠራ አንተ ትጠ​ባ​በ​ቀ​ኛ​ለህ፤ ከኀ​ጢ​ኣ​ቴም ንጹሕ አታ​ደ​ር​ገ​ኝም።


በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።


አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን።


አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።


እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! በኀ​ጢ​አ​ትህ ወድ​ቀ​ሃ​ልና ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ።


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


ወይን የሰ​ውን ልብ ደስ ያሰ​ኛል፥ ዘይ​ትም ፊትን ለማ​ብ​ራት ነው። እህ​ልም የሰ​ውን ኀይል ያጠ​ነ​ክ​ራል።


ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አል​ሁት፤ ትሎ​ች​ንም እና​ንተ እና​ቴም ወን​ድ​ሞቼም ናችሁ አል​ኋ​ቸው።


ከጭቃ እንደ ፈጠ​ር​ኸኝ አስብ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ትቢያ ትመ​ል​ሰ​ኛ​ለህ፤


የሚ​ያ​የኝ ሰው ዐይን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​የ​ኝም፤ ዐይ​ንህ በእኔ ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አል​ገ​ኝም።


አሁ​ንም ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ቼም ባረ​ፍሁ ነበር፤


ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


ሰው​ነ​ቶቼ ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ፤ እን​ግ​ዲህ ንጹሕ አድ​ር​ገህ እን​ደ​ማ​ት​ተ​ወኝ አው​ቃ​ለሁ፥


አሁን ፈጽሜ ዝም እል ዘንድ፥ ከእኔ ጋር የሚ​ፋ​ረድ ማን ነው?


ባለ​ጠጋ ይተ​ኛል፥ የሚ​ያ​ነ​ቃ​ውም የለም፤ ዐይ​ኖ​ቹን ይከ​ፍ​ታል፥ ይደ​ነ​ቃ​ልም።


እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።


ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።


እንደ ሕልም ይበ​ር​ራል፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም፤ ሲነ​ጋም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰ​ደ​ዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios