La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ድምፄንም አልሰሙምና፥ በእርሱም አልተመላለሱምና፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 9:13
11 Referencias Cruzadas  

“እና​ንተ ግን ብት​መ​ለሱ፥ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ብት​ተዉ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥


አሁ​ንስ ከዚህ በኋላ ምን እን​ላ​ለን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ትተ​ና​ልና።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በክፉ ልባ​ቸ​ውም እል​ከ​ኝ​ነት የሚ​ሄዱ፥ ያገ​ለ​ግ​ሏ​ቸ​ውና ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸው ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ት​ለው የሚ​ሄዱ እነ​ዚህ ክፉ ሕዝብ አን​ዳች እን​ደ​ማ​ት​ረባ እን​ደ​ዚች መታ​ጠ​ቂያ ይሆ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም፦ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመ​ለ​ኳ​ቸ​ውም ነው ብለው ይመ​ል​ሳሉ።”


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ነገር ግን አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጉት ይልቅ የባሰ አደ​ረጉ።