La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልባ​ች​ሁን ታም​ማ​ችሁ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዛ​ላ​ችሁ። ከሚ​ያ​ቅ​በ​ዘ​ብዝ የልብ ሕመ​ማ​ችሁ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ የለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መጽናናት የማይገኝለት ብርቱ ሐዘን ደርሶብኛል፤ ልቤም እጅግ ዝሎአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 8:18
12 Referencias Cruzadas  

እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥


ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።


ስለ ነቢ​ያት ልቤ በው​ስጤ ተሰ​ብ​ሮ​አል፤ አጥ​ን​ቶ​ችም ሁሉ ታው​ከ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤ ከጌ​ት​ነ​ቱም ክብር የተ​ነሣ እኔም በመ​ከራ እንደ ተቀ​ጠ​ቀጠ ሰው፥ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ሸ​ነ​ፈ​ውም እንደ ሰካ​ራም ሰው ሆኛ​ለሁ።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


ስለ​ዚህ ልባ​ችን ታም​ሞ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይ​ና​ችን ፈዝ​ዞ​አል፤


እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።