ኤርምያስ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የፈረሶቻቸው ድምፅ ከዳን ተሰማ፤ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፤ መጡም ምድሪቱንና በእርሷም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን እስከ ዳን ከተማ ደርሰዋል፤ ፈረሶቻቸው ሲያንኮራፉ ድምፃቸው ይሰማል፤ ሰንጋ ፈረሶቻቸውም ሲያሽካኩ ምድር ትናወጣለች፤ ጠላቶቻችን የመጡት ምንም ሳያስቀሩ ሕዝባችንንና ከተሞቻችንን እንዲሁም በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈረሰኞቹ ድምጽ ከዳን ተሰማ፥ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፥ መጡም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ። |
ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ ላይ መዓትህን አፍስስ።
ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችንን ሥራ፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል።
ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
ከኀይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው አይመለሱም።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም፥ ዘይትህንም ይበላሉ፤ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችህንም በሰይፍ ያጠፋሉ።”
ቀስትና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፤ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።
ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር ዐሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች፤ ታመመችም።
ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል።
እንግዲህ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ያላችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገራችሁና ባልንጀራችሁም የሚጠራጠር ስለሆነ አትብሉ።
ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ የከተማዪቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።