La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አቅኑ፤ በዚ​ህም ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 7:3
18 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁት፥ በባ​ሪ​ያ​ዎቼ በነ​ቢ​ያት የላ​ክ​ሁ​ላ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ሕጌ​ንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነ​ቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ መሰ​ከረ።


አሁ​ንም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አድ​ርጉ፤ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛ​ብና ከእ​ን​ግ​ዶች ሴቶች ተለዩ” አላ​ቸው።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታ​ትና መሳ​ፍ​ንት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ እየ​ተ​ቀ​መጡ በዚ​ህች ከተማ በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱና አለ​ቆ​ቻ​ቸው የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ቀ​መጡ ይገ​ባሉ፤ ይህ​ችም ከተማ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች።


አሁን እን​ግ​ዲህ ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈ​ጥ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ምክ​ር​ንም እመ​ክ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ሁላ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁ​ንም አቅኑ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው።”


ስለ እነ​ርሱ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸው ሕዝብ ከክ​ፋ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ካሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር እጸ​ጸ​ታ​ለሁ።


አሁ​ንም መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አሳ​ምሩ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ች​ሁን ክፉ ነገር ይተ​ዋል።


ደግ​ሞም፦ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ሥራ​ች​ሁ​ንም አሳ​ምሩ፤ ታገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ሁት ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ እያ​ልሁ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ችሁ ነበር፤ እና​ንተ ግን ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።


የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳብ ልጆች አባ​ታ​ቸው ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ትእ​ዛዝ ፈጽ​መ​ዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አል​ሰ​ማ​ኝም፤


እስ​ራ​ኤል ወደ እኔ ቢመ​ለስ ይመ​ለስ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ርኵ​ሰ​ቱ​ንም ከአፉ ቢያ​ስ​ወ​ግድ፤ ከፊ​ቴም የተ​ነሣ ቢፈራ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።