ኤርምያስ 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወናፉን የሚአናፋው ደከመ፤ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፤ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል፤ ኀጢአታቸውም አልተወገደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርሳሱን ለማቅለጥ፣ ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወናፉ በኃይል አናፋ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፤ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል ነገረ ግን ኃጢአተኞች አልተወገዱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሳሱን በእሳት ለማቅለጥ ወናፉ በኀይል ያናፋል፤ ክፉዎች ስላልተወገዱ ግን አንጥረኛው በከንቱ ይደክማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወናፉ አናፋ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፥ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል፥ ኃጢአተኞች አልተወገዱም። |
እኔ ግን፥ “በከንቱ ደከምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ይፈርድልኛል፤ መከራዬም በአምላኬ ፊት ነው” አልሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ፤ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እንደዚሁ አደርጋለሁና።
በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፤ አነጻሁሽ፤ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ለእናቱም ገንዘቡን መለሰላት እናቱም ብሩን ወስዳ ከእርሱ ሁለቱን መቶ ብር ለአንጥረኛ ሰጠችው፤ እርሱም የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አደረገው። በሚካም ቤት አስቀመጡት።