Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 49:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጕልበቴን ጨረስሁ፤ ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እኔ ግን “በከንቱ ለፋሁ፤ ያለ ጥቅም በከንቱ ጒልበቴን አባከንሁ፤ ሆኖም ጉዳዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የድካሜም ዋጋ ከአምላኬ ጋር ነው” አልኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እኔ ግን፦ በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፥ ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 49:4
28 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ አእ​ምሮ የሌ​ላ​ችሁ፥ ልቡ​ና​ች​ሁን አረ​ጋጉ፤ ጽኑ፤ አት​ፍሩ፤ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ፍር​ድን ይመ​ል​ሳል፤ ይበ​ቀ​ላ​ልም፤ እር​ሱም መጥቶ ያድ​ነ​ናል።


ስለ እና​ንተ በከ​ንቱ ደክሜ እንደ ሆነ ብዬ እፈ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


በሚ​ድ​ኑ​ትና በሚ​ጠ​ፉት ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ር​ስ​ቶስ መዓዛ እኛ ነንና።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


ኢየሱስም መልሶ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት፤” አለ።


ነገር ግን አንተ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብት​ገ​ሥ​ጸው እር​ሱም ከኀ​ጢ​አ​ቱና ከክፉ መን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።


እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ምድር ዳርቻ አዋጅ እን​ዲህ ብሎ ነግ​ሮ​አል፥ “ለጽ​ዮን ልጅ፦ እነሆ፥ መድ​ኀ​ኒ​ትሽ ይመ​ጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእ​ርሱ ጋር ሥራ​ውም በፊቱ አለ በሉ​አት።”


እነሆ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይሉ ይመ​ጣል፤ በክ​ን​ዱም ይገ​ዛል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእ​ርሱ ጋር ሥራ​ውም በፊቱ ነው።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ግን “ሁል​ጊዜ ከዳ​ተ​ኞ​ችና ወን​ጀ​ለ​ኞች ወደ​ሆ​ኑት ሕዝብ እጄን ዘረ​ጋሁ” ብሎ​አል።


ወደ ወገ​ኖቹ መጣ፤ ወገ​ኖቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።


ክር​ስ​ቶስ እን​ዲህ ይሞት ዘንድ ወደ ክብ​ሩም ይመ​ለስ ዘንድ ያለው አይ​ደ​ለ​ምን?”


በጽ​ድቅ መን​ገድ ወደ​ማ​ይ​ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ወደ​ሚ​ከ​ተሉ ዐመ​ፀ​ኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆ​ችን ዘረ​ጋሁ።


ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።


የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ መን​ገዴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተሰ​ው​ራ​ለች፤ አም​ላ​ኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍር​ዴ​ንም ትት​ዋል፤ ለምን ትላ​ለህ? ለም​ንስ እን​ዲህ ትና​ገ​ራ​ለህ?


ለኃ​ጥ​አን ደስታ የላ​ቸ​ውም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ያዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ የበ​ቀ​ልና የፍ​ዳን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጐ​ና​ጸፈ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።


ኤል​ያ​ስም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios