እነሆ፥ ዛሬ ከምድር ፊት ከአሳደድኸኝ፥ ከፊትህ እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”
ኤርምያስ 52:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ የእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው። ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፥ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። |
እነሆ፥ ዛሬ ከምድር ፊት ከአሳደድኸኝ፥ ከፊትህ እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”
ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
እግዚአብሔርም በእስራኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አፍ እንደ ተናገረው እስራኤልን ከፊቱ እስኪያወጣ ድረስ ከእርስዋ አልራቁም። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከምድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።
ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
ደግሞም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ፤ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዐመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጎዳች፥ ከጥንቱም የገባሮች ሽፍትነት በእርስዋ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፤ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።
ግብፃውያንንም በጨካኝ ጌቶች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኞች ነገሥታትም ይገዟቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ኀይለኛውን ወንድና ኀይለኛዋን ሴት፥ የእንጃራን ኀይል ሁሉ፥ የውኃውንም ኀይል ሁሉ ያስወግዳል፤
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።