ኤርምያስ 52:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመተ መንግሥት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በዐምስተኛው ወር፤ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዓሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚያገለግለው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር በዐሥረኛው ቀን የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ የሆነው ናቡዛርዳን ኢየሩሳሌም ገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በአሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። |
የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ ከአስቈጡ በኋላ በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ።
ንጉሡንም፥ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር፤ የአባቶች መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አያዝን?” አልሁት።
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
ይችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን ይመጣሉ፤ ከተማዋንም በእሳት ያነድዱአታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ያጠኑባቸውን፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸውን ቤቶች ያቃጥሉአቸዋል።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።