እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
ኤርምያስ 51:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎንን ምስሎች የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፤ ምድርዋም ሁሉ ትደርቃለች፤ ተዋግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣ በርግጥ ይመጣልና። ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤ የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ያፈረች ትሆናለች ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የባቢሎንን ጣዖቶች የማስወግድበት ጊዜ ይመጣል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ኀፍረት ይደርሳል፤ የተገደሉባት ልጆችዋ ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፥ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ። |
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
“ለአሕዛብ ተናገሩ፤ አውሩም፤ ዓላማውንም አንሡ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮዳክ ፈራች፤ ምስሎችዋም አፈሩ፤ ጣዖታቷም ደነገጡ፤ በሉ።
በጽዮን በዐይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እበቀላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ።