ኤርምያስ 51:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚገፋሽን እፈርድበታለሁ፤ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፤ ምንጭዋንም አደርቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እሟገትልሻለሁ፣ በቀልሽንም እኔ እበቀልልሻለሁ፤ ባሕሯን አደርቃለሁ፣ የምንጮቿንም ውሃ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፥ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ። |
የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፤ ስደተኞችን አስነሣለሁ፤ ከለዳውያንም በመርከብ ውስጥ ይታሰራሉ።
እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በደሴቶችዋ ይመካሉና ሰይፍ በውኆችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደርቃሉ።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ፤ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
ሰማያት ሁሉ በአንድነት ደስ ይላቸዋል፤ የእግዚአብሔርም መላእክት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ከሕዝቡ ጋር ደስ ይላቸዋል። የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የልጆቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ለሚጠላቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋልና፥ እግዚአብሔርም የሕዝቡን ምድር ያነጻል።”