Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 44:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ጥልቁን ውሃ፣ ‘ደረቅ ሁን፤ ወንዞችህን አደርቃለሁ’ እላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ውቅያኖሱን ‘እኔ ወንዞችህን ስለማደርቅ አንተ ድረቅ’ እለዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ቀላዩም፦ ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ እላለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 44:27
14 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤


ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


ተራ​ሮ​ች​ንና ኮረ​ብ​ቶ​ችን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ቡቃ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ደሴ​ቶች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ኩሬ​ዎ​ች​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።


በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦


እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አል​ነ​በ​ረም፤ ተጣ​ራሁ፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ እጄ ለማ​ዳን ጠን​ካራ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ ለማ​ዳን አል​ች​ል​ምን? እነሆ፥ በገ​ሠ​ጽሁ ጊዜ ባሕ​ርን አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ውኃም በማ​ጣት ዐሣ​ዎ​ቻ​ቸው ይሞ​ታሉ፤ በጥ​ማ​ትም ያል​ቃሉ።


ባሕ​ርን የማ​ና​ውጥ፥ ሞገ​ዱም እን​ዲ​ተ​ምም የማ​ደ​ርግ አማ​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚ​ገ​ፋ​ሽን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ በቀ​ል​ሽ​ንም እበ​ቀ​ል​ል​ሻ​ለሁ፤ ባሕ​ር​ዋ​ንም ድርቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ምን​ጭ​ዋ​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።


እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል።


ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos