ኤርምያስ 51:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር ዐሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች፤ ታመመችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በዚያ መኖር እስከማይችል ድረስ፣ የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደው ስለሚጸና፣ ምድር ትናወጣለች፤ በሥቃይም ትወራጫለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ የጌታ አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች ተወራጨችም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎንን ማንም የማይኖርባት ምድረ በዳ እንድትሆን ለማድረግ እግዚአብሔር ያቀደውን የሚፈጽምበት ጊዜ ከመሆኑ የተነሣ፥ ምድር በመናወጥ ትንቀጠቀጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናውጣለች ታመመችም። |
ምድር በወይን እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ ሕግን መተላለፍዋም ይከብድባታል፤ ትወድቅማለች፤ ደግማም አትነሣም።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ በእውነት የበጎቻቸቸው ጠቦቶች ይጠፋሉ፤ በእውነት ማደሪያዎቻቸውም ባድማ ይሆናሉ።
ከአንተም ለማዕዘን የሚሆን ድንጋይንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይን አይወስዱም፤ ለዘለዓለምም አጠፋሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
ምድሪቱም ከፊታቸው ትደነግጣለች፤ ሰማይም ይንቀጠቀጣል፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።
በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ጦርነት እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ እንደ ግብፅም ወንዝ ይሞላል፤ ደግሞም ይወርዳል።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤