ኤርምያስ 51:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ፍርዳችንን አውጥቶአል፤ ኑ በጽዮን የአምላካችን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እግዚአብሔር ቅንነታችንን መሰከረ፤ ኑ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ያደረገውን፣ በጽዮን እንናገር።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጽድቃችንን በግልጥ አውጥቶአል፤ ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የጌታን ሥራ እንናገር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን እንዲህ ተባባሉ፦ “እግዚአብሔር ለእኛ ትክክለኛ ፍርዱን ስለ ሰጠን ኑ! ወደ ኢየሩሳሌም ሄደን እግዚአብሔር አምላካችን ያደረገውን ሁሉ እንናገር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል፥ ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር። |
ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፤ በምድር የቀሩትም ስለ እግዚአብሔር ክብር በአንድነት ደስ ይላቸዋል፤ የባሕርም ውኃ ይናወጣል።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ ወደ ጽዮንም በደስታና በሐሤት ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ክብር በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፤ ኀዘንና ልቅሶም ይወገዳሉ።
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፥ የመቅደሱንም በቀል፥ በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን ሀገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።
ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ በእውነት የበጎቻቸቸው ጠቦቶች ይጠፋሉ፤ በእውነት ማደሪያዎቻቸውም ባድማ ይሆናሉ።