ኤርምያስ 50:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዶምንና ገሞራን፥ በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም፤ የሰውም ልጅ አይኖርባትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣ በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀረኋቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዶምንና ገሞራን በአካባቢያቸው ካሉ ከተሞች ጋር በደመሰስኩ ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም በባቢሎን ማንም እንደገና ሰፍሮ መኖር አይችልም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። |
ሰዶምና ገሞራ፥ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፥ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር፤ እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም፤ የሰው ልጅም አይኖርባትም።
ከአንተም ለማዕዘን የሚሆን ድንጋይንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይን አይወስዱም፤ ለዘለዓለምም አጠፋሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሰዶምንና ገሞራን አስቀድሜ እንደ ገለበጥኋቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፤ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ በዚህም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
ኢሳይያስም አስቀድሞ እንደ ተናገረ “እግዚአብሔር ጸባኦት ዘር ያስቀረልን ባይሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።