Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 50:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣ በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀረኋቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሰዶምንና ገሞራን በአካባቢያቸው ካሉ ከተሞች ጋር በደመሰስኩ ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም በባቢሎን ማንም እንደገና ሰፍሮ መኖር አይችልም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ ሰው በዚያ አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰ​ውም ልጅ አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:40
15 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ኃጢአትንም እያደረጉ ላሉት ምሳሌ እንዲሆን፤ የሰዶምንና ገሞራን ከተማዎች አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ከፈረደባቸው፥


ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ጎረቤቶቻቸው እንደ ተገለባበጡ፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።


በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፤ እርሷም በምሳሌያዊ አነጋገር ሰዶምና ግብጽ የተባለችው፥ ጌታቸውም የተሰቀለባት ከተማ ናት።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።


“ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘለዓለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል ጌታ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፤ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።


ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


ደግሞም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን ነበር፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር” ብሎ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios