“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ኤርምያስ 50:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የዱር አራዊት ከተኵላዎች ጋር ይቀመጡባታል፤ ሰጎኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘለዓለም አይቀመጥባትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣ የጕጕትም ማደሪያ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በባቢሎን የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘለዓለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ የዱር አራዊት ከቀበሮችና ከሰጎኖች ጋር በባቢሎን ይኖራሉ፤ እንዲሁም እስከ መቼም ድረስ ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ አትሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፥ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም። |
“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
ሕዝቤ ከሰሜን በእርስዋ ላይ ወጥትዋል፤ ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
ከአንተም ለማዕዘን የሚሆን ድንጋይንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይን አይወስዱም፤ ለዘለዓለምም አጠፋሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤