ኤርምያስ 50:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር በባቢሎን ላይ በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ስለ ባቢሎንና ስለ ባቢሎናውያን ምድር፣ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ባቢሎንና ስለ ሕዝብዋ እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። |
ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ።
ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
የአሦርም ንጉሥ ከባቢሎንና ከኩታ፥ ከአዋና ከሐማት፥ ከሴፌርዋይም ሰዎችን አመጣ፤ በእስራኤልም ልጆች ፋንታ በሰማርያ ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት፤ በከተሞችዋም ተቀመጡ።
እርሱም ገና ይህን ሲናገር ሦስተኛው መልእክተኛ መጥቶ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “ፈረሰኞች በሦስት ረድፍ ከብበው ግመሎችን ማርከው ወሰዱ፥ ብላቴኖችህንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።”
ይህንም ሙሾ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፤ እንዲህም ትላለህ፥ “አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
ከዚህም በኋላ ከከለዳውያን ሀገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እናንተ ወደ አላችሁባት ወደዚች ሀገር አመጣው።