ኤርምያስ 46:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ጫኑና ውጡ፤ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ፤ ጥሩርንም ልበሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ! የራስ ቍር ደፍታችሁ፣ በየቦታችሁ ቁሙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁን ልበሱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈረሰኞች ሆይ! ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፥ ራስ ቁርንም ደፍታችሁ በቦታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሶቻችሁን ለጒማችሁ ርካብ ረግጣችሁ ውጡ፤ የራስ ቊር ደፍታችሁ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ የጦር ልብሳችሁንም ልበሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ፥ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ፥ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ። |
ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስትና ጥሩርም ይዘው በፊትና በኋላ ይጠብቁ ነበር፤ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።
አሕዛብ ሆይ፥ ዕወቁና ደንግጡ፤ እስከ ምድር ዳርቻም ስሙ፤ ኀያላን! ድል ሁኑ፤ ዳግመኛም ብትበረቱ እንደ ገና ድል ትሆናላችሁ።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
በቀስት ወርዋሪው ላይ፥ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፤ ለጐበዛዝቷ አትዘኑ፤ ሠራዊቷንም ሁሉ አጥፉ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመግደል ተመዝዞአል፤ ጨርሶም ያርድ ዘንድ ተሰንግሎአል በል።