በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
ኤርምያስ 4:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ ይላል፦ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እግዚአብሔር፥ ምድሪቱ ወደ ምድረ በዳነት እንደምትለወጥ፥ እስከ መጨረሻው ግን እንደማይደምስሳት ተነግሮአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም። |
በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፥ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ያጠፋታል፤ ባድማም ያደርጋታል፤ ይገለብጣትማል፤ በእርስዋም የተቀመጡትን ይበትናል።
አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥” ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።”
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
ስለዚህ መዓቴና መቅሠፍቴ ወረደ፤ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።
አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም ያሳደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።”
“ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የእግዚአብሔር ናቸውና መጠጊያዎችዋን አትርፉ።
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ዛይ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ጣለ፤ መቅደሱንም ጠላው፤ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ድምፃቸውን በዕልልታ አሰሙ።
ትንቢትም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! ወዮልኝ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?” ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።
ምድሪቱንም ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ፤ የኀይልዋም ስድብ ይቀራል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤ ማንም አያልፍባቸውም።
እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፤ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም መዓዛ አላሸትትም።
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም፤ አልጸየፋቸውምም።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።