ኤርምያስ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድር ሁሉ ተዋርዳለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ ጠፋ፤ መጋረጃዎችም ተቀዳደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ ድንኳኔ በድንገት፣ መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድሪቱም ሁሉ ጠፍታለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በዐይን ቅጽበትም መጋረጃዎቼ ጠፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፥ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፥ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለእስራኤል ልጆች እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅሠፍት እንዳላመጣባችሁና እንዳላጠፋችሁ ተጠንቀቁ፤ አሁንም የክብር ልብሳችሁንና ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ፤ የማደርግባችሁንም አሳያችኋለሁ በላቸው” አለው።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች በድንገት ይመጡብሻል፤ የወላድ መካንነትና መበለትነት ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽንም ዘርጊ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስሞችሽንም ትከዪ።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ መቅሠፍቶችን፥ ሰይፍንና ራብን፥ ክፉዎችንም አውሬዎች፥ ቸነፈርንም ስሰድድባት፥
“ከዚያም በኋላ በእንቢተኝነት ብትሄዱብኝ፥ ልትሰሙኝም ባትፈቅዱ እንደ ኀጢአታችሁ መጠን በመቅሠፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።