በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
ኤርምያስ 39:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ሰውነትህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በእኔ ታምነሃልና፥” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እታደግሃለሁ፤ በእኔ ታምነሃልና በሕይወት ታመልጣለህ እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጽሜ አድንሃለሁ፥ ነፍስህም ለአንተ በምርኮ ትድናለች እንጂ በሰይፍ አንተ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል ጌታ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በሰላም ስለምጠብቅህ አትሞትም፤ በእኔ ስለ ታመንክ በሕይወት ትተርፋለህ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
ጥበብን አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥ እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥ በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
በዚህች ከተማ ውስጥ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል፤ ሰውነቱም ምርኮ ትሆናለች።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል፤ ነፍሱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤ በሕይወትም ይኖራል።