ኤርምያስ 39:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ውሰደውና በመልካም ተመልከተው፤ የሚልህንም ነገር አድርግለት እንጂ ክፉን ነገር አታድርግበት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ውሰደውና እንክብካቤ አድርግለት፤ የሚፈልገውን ነገር ፈጽምለት እንጂ አትጕዳው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ውሰደው፥ በበጎ ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አታድርግበት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሂድ፥ ኤርምያስን ፈልገህ አግኘውና ተገቢውን ጥንቃቄ አድርግለት፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ አድርግለት እንጂ በምንም ነገር እንዳትጐዳው።” |
አቤቱ! በመከራቸውና በጭንቃቸው ጊዜ በጠላቶቻቸው ዘንድ ስለ እነርሱ በጎ ነገር በአንተ ፊት የቆምሁ ባልሆን ይህ ለእነርሱ መከናወን ይሁን።
ዐይኔንም ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር ለመልካም እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።
የአዛዞች አለቃ ናቡዛርዳንም ላከ፤ ናቡሻዝባንም፥ ራፋስቂስም፥ ኔርጋል ሴራአጼርም፥ ራብማግም፥ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ ላኩ።
አሁንም እነሆ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፤ እኔም በመልካም አይሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፤ ተመልከት፥ እነሆ፥ ሀገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ በሚታይህና ደስ በሚያሰኝህም ስፍራ ተቀመጥ።”
በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ በዚያ ሰይፍን አዝዛታለሁ፤ እርስዋም ትገድላቸዋለች፤ ዐይኔንም ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እጥላለሁ።”
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።